ማዕከሉ በኮንትራት ለቀጠራቸው የጥበቃ ሠራተኞች...

image description
image description
image description
- Recent News   

ማዕከሉ በኮንትራት ለቀጠራቸው የጥበቃ ሠራተኞች ማብራሪያ ሰጠ

የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በቅርቡ ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድረው ላለፉ የጥበቃ ሠራተኞች ማብራሪይ ሰጠ፡፡በመድረኩ ተገኝተው ማብራሪያውን የሠጡት የማዕከሉ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ አበበ እና የጥበቃ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ክንፈ ገብረማሪያም ናቸው፡፡ በመድረኩ የዕፅዋት ማዕከሉ ዓላማዎች፣ራዕይ፣ተልኮ እና እሴቶች የተነሱ ሲሆን እነሱንም ለማሳካት ማዕከሉ ከተቋቋመ ጀምሮ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት በሰፊው ተብሯርቷል፡፡እንዲሁም ከተቀጣሪ ሠራተኞቹ የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት፣ መብትና ግዴታም በዝርዝር የተገለፀ ሲሆን በተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ ማዕከሉ ባደረገው የኮንትራት ቅጥር ለ60 ወገኖች የስራ ዕድል መፍጠሩ ታውቋል፡፡