ወርቃማው ሰኞ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተካሄደ
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በወርቃማው ሰኞ መድረክ የህይወት ተሞክሮዎችን የሚያካፍልበት መድረክ ነው፡፡
የዛሬውን የወርቃማ ሰኞ የህይወት ተሞክሮ እርስ በእርስ የምንማማርበት እና ጠቀሜታውም ላቅ ያለ መሆኑን በመግለጽ መድረኩን የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞገስ አባተ አስጀምረዋል፡፡
በመቀጠል የዕለቱን መልዕክት በማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ዳይሬክቶሬት የእንግዳ ቅበላ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አበበ ስንታየሁ ነገሮችን ካለመሞከር የምናጣውን እና በድፍረት ብናደርጋቸው የምናገኘውን ጥቅም በማነጻጸር አቅርበዋል፡፡
አቶ አበበ በህይወት ጉዞአቸው ውስጥ ሳይሞክሯቸው የቀሩትን ፀፀት በማለት የገለጹ ሲሆን ለምን እንፈራለን ብለው ላነሱት ጥያቄ አሉታዊ ትንበያ ፤ የደህንነት ቀጠና እና አለመሳካትን እንደ ማንነት መውደቅ ማየት የሚሉትን ምክንያቶች በዋናነት በመጥቀስ "አለም የሚሞክሩ ሰዎች ውጤት ናት" የሚለውን የኦሾን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር በቀረበው ርዕስ ላይ አስተያየት የተቀበሉ ሲሆን በእለቱ ከቀረበው መልዕክት ብዙ እንደምንማርና ለወደፊት በህይወታችን ልንተገብረው እንደሚገባ የማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ በሰጡት አስተያየት የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል፡፡