የአለም የሴቶች ቀን በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ተከ...

image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

የአለም የሴቶች ቀን በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ተከበረ

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት የአለም የሴቶች ቀን  "የሴቶች ድምጽ ለእኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጲያ" በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ለ115 ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጲያ ለ50ኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡ 

የኢትዮጲያ ሴቶች የ50 አመታት የለውጥ ጉዞ እና የማርች 8 ታሪካዊ ፋይዳ በሚል ርዕስ የቀረበውን ሰነድ የማዕከሉ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የመረጃ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ማርታ እንዳይላሉ አቅርበዋል ፡፡ 
በሰነዱ ውስጥ የማርች 8 አጀማመር ፤ የሴቶች ፈተና ፤ በከፍተኛ አመራርነት የተመዘገቡ ስኬቶች፤ የከንቲባ አዳነች አበቤ አርአያነት እና ተሞክሮ ፤ በሀገራችን ሴቶች እና ኮሪደር ልማት፤ የሴቶች ተጠቃሚነት ከፋይናንስ እና ከማህበራዊ ልማት አኳያ፤ እና በቀጣይ ሴቶችን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተብለው የተለዩ የአመለካከት ለውጥ ላይ መስራት ፣ስራን ሳያማርጡ መሳተፍ እና ግንዛቤ መፍጠር ስራ ማጠናከር ቤተሰብና ማህበረሰብ ሚናቸውን እንዲወጡ ማድረግ ጥቃት ሲፈፀም ዝም አለማለትና አጥፊዎችን ማጋለጥ የሚሉ ርዕሶች ተካተዋል፡፡ 
በመቀጠል ማርች 8 የሴቶች ሁለንተናዊ የትግል እንቅስቃሴና ውጤት የምንዘክርበት ታሪካዊ ቀን በመሆኑ ቀኑ በየአመቱ ሲከበር ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም አጋርነታቸውን በማጠናከር ለሴቶች መብት መከበርና የእኩል ተጠቃሚነት ስርዓት ፆታ እኩልነት መስፈን በጋራ በመሆን የሚሰሩበትና የሚዘክሩበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም መድረኩን የማዕከሉ የኦዲት ዳይሬክተር ወ/ሮ አየለች ባየልኝ እና እና የኢኮቱሪዝም ዳይሬክቶሬት የገበያ ጥናት ቡድን መሪ በሆኑት ወ/ት አሊፋት አስፍር ከሰራተኛው የተነሱትን ሀሳብ እና አስተያየት በመቀበልና ምላሽ በመስጠት የዕለቱን መድረክ ተጠናቋል፡፡