በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባለሙያዎች በኩል ከሪፎርም እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ክትትልና ድጋፍ ተደረገ
የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ዓላማ ፈጻሚዎች እና የደጋፊ የስራ ሂደቶችን ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት ድጋፍ እና ክትትል ተደረገ፡፡
በክትትል እና ድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ልማት ዘርፍ ም/ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ ሲሆኑ ይህ ክትትል እና ድጋፍ በቀጣይ ለምንሰራቸው ስራዎች መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖርውና ለሚደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን በማስተላለፍ ፕሮግራሙን አስጀምረዋል፡፡
በመቀጠል ክትትል እና ድጋፉን ከፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ቢሮ በመጡት ወ/ሮ መሰረት ወንደሜነህ እና አቶ ጌታቸር በላቸው ያከናወኑ ሲሆን ከማዕከሉ የአላማ ፈጻሚዎች እና ደጋፊ የስራ ክፍሎች የተለያዩ ማስረጃዎችን እና ሰነዶችን በመመልከት በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች በማንሳት ከማኔጅመንት አባላቱ ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም የማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደባላ ብሩ ድጋፍ እና ክትትሉ ማዕከሉን በቀጣይ ለሚሰራቸው ስራዎች የሚያግዝ መሆኑን በመግለጽ ሃሳባቸውን በመስጠት የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡