የብዝሀ-ሕይወት ትምህርት ተሰጠ፡፡
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ከለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመጡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በተግባር የተደገፍ የብዝሀ-ሕይወት ትምህርት ሰጠ፡፡ የማዕከሉ የብዝሀ-ህይወት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ቁጥራቸው 53 ለሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርቱን በተግባር ሰጥተዋል፡፡
በዚህም አበባ ያላቸው ከሌላቸው እንዴት ይለያሉ፣የመከለያ ቤት ጠቀሜታው፣ ስለበረሀማ ዕፅዋት ምንነት፣ ስለችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የዕፅዋት ብዜትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ባለሙያዎቹ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተማሪዎቹ በኩል ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፡: