ወርቃማው ሰኞ በአንድነትና በንቁ ተሳትፎ ተካሄደ
ዛሬ የ“ወርቃማው ሰኞ” መድረክ በከፍተኛ ተሳትፎና በልዩ እንቅስቃሴ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የማዕከሉ ሰራተኞች ልምዳቸውን በመጋራት፣ አዳዲስ ሀሳቦችን በማቅረብ እና በአንድነት ግቦቻቸውን በመግለጽ የሚሳተፉበት ሲሆን ይህም በስራ ውጤታማነት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዲኖር ያደርጋል።
የዛሬውን የወርቃማ ሰኞ መድረክ የማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደበላ ብሩ ይህ መድረክ አዲስ ሳምንትን በአዎንታዊ ኃይል ለመጀመር፣ ተሳታፊዎችን ለስኬት ለመነሳሳት እና የስራ እቅዶችን በተቀናጀ መንገድ ለማስጀመር አስፈላጊ ሚና ተጫውቷል “ወርቃማው ሰኞ” እንደ ተለመደው የተስፋና የተነሳሽነት መድረክ ሆኖ ቀጥሎ ይካሄዳል በማለት አስጀምረዋል፡፡
በመቀጠል የዕለቱን ወርቃማ ሰኞ መልዕክት ወ/ሮ አየሉ ሰማኝ በክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የውጪ ሀገር ጉብኝት ተሞክሮ መነሻ በማድረግ ወደ ከተማችን በማምጣት ቢተገበር ይጠቅማል አብሮነትን ያጎለብታል ፤ ቅርበትን ይጨምራል ፤ ልምድ ይወሰድበታል በማለት በ2017 ዓ.ም መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ አየሉ በህይወታቸው ያሳለፏቸውን የህይወት ተሞክሮ ለሰራተኛው ሊጠቅም በሚችል መልኩ ያቀረቡ ሲሆን በተሞክሯቸውም ከዝቅተኛ ስራ ድርሻ እስከ ስራ ሂደት አመራር የደረሱት ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በፅናት በማለፍ እንደሆነ ጭምር ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ በሰጡት አስተያየት አንድ ሰው የውስጥ ጥረት እና በህይወቱ ውስጥ ለመለወጥና ወደተሻለ ደረጃ ለመድረስ ፍላጎት ካለው አሸናፊ እና በተሰማራበት የስራ መስክም ውጤታማ እንደሚሆን በመግለጽ የዕለቱን መድረክ ተጠናቋል፡፡