ለማዕከሉ የቀን ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለማዕከሉ የቀን ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ስልጠናውን የማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደበላ ብሩ ያስጀመሩ ሲሆን በመክፈቻው ላይም ማዕከሉ ከያዛቸው ዓላማዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና አጠቃቀም መሆኑን በመግለጽ ማዕከሉ ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍል የስራ እድል የፈጠረ እንደመሆኑ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ለሆኑት በስራቸው ላይ ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት አቅማቸውን ለማጎልበት እና በቀጣይ የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት እንዲችሉ በዕፅዋት ብዜት፣ በአፈር እና ውሀ ጥበቃ እና በገጸ ምድር ማስዋብ ስራ ለተሰማሩ ሰራተኞችየተዘጋጀውን ስልጠና አስጀምረዋል፡፡
በመቀጠል የማዕከሉ የሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መክብብ ማሞ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የታቀደውን አንድ ሚሊዮን የውበት እና የሀገር በቀል ዕፅዋት ብዜት ለማከናወን የሚቻለው በስራው ላይ የሚገኙትን ሰራተኞች የስራ ስምሪት በመስጠት እና በቂ ክህሎት እንዲኖራቸው በአፈር እና ጥበቃ ፣በዕፅዋት ብዜት ፣ በከተማ ግብርናን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን እንዲቻል ስልጠናውን በሁለት ዙር ለ140 የቀን ሰራተኞች መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን በሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች አቶ አበበ በየነ (የዕፅዋት ልማት ቡድን) ፣ አቶ ቢራራ ሙጬ( የላንድስኬፕ ዲዛይን ባለሙያ) ፣ አቶ መዳን ኪዳኔ(የተፈጥሮ ሀብት ባለሙያ) እንዲሁም አቶ ደርበ አበባው (ጀማሪ ተመራማሪ) በተግባር እና በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የተሰጠ ሲሆን በስልጠናወ ላይ ከተሳተፉት ሰልጣኞች የተነሱትን ጥያቄዎች ባለሙያዎቹ ሙያዊ ማብራሪያዎችን በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡