በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የተግባር ተኮር ትምህርት ለተማሪዎች ተሰጠ
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለመጡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የተግባር ተኮር ትምህርት ሰጠ፡፡ ተማሪዎቹ ከአገሪ ቱሉ ፣ከምዕራፍ እና ከድልበር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጡ ሲሆን በተግባር የተደገፍ የብዝሀ-ሕይወት ትምህርት በማዕከሉ የብዝሀ-ህይወት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዩሀንስ መላኩ ተሰጥቷል፡፡
በዚህም አበባ ያላቸው ዕፅዋት ከሌላቸው እንዴት ይለያሉ፣ መከለያ ቤት ጠቀሜታው፣ ስለበረሀማ ዕፅዋት ምንነት፣ ስለችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የዕፅዋት ብዜትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ ሲሆን በተማሪዎቹ በኩል ለተነሱ ጥያቄዎችም ዳይሬክተሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡