ወርቃማው ሰኞ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተካሄደ

image description
image description
image description
image description
- Recent News   

ወርቃማው ሰኞ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተካሄደ

የዛሬውን ውይይት መድረክ የማዕከሉ የምርምርና ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ ወርቃማው ሰኞ በማህበራዊ ግንኙነት መጠናከርና በልምድ መማር ላይ ያተኮረ መሆኑን በመግለጽ መድረኩን ከፍተዋል፡፡

በመቀጠል የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የፋሲሊቲ አገልግሎት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ መሰለ የህይወት ታሪካቸውን በመካፈል ለተሳታፊዎች ትልቅ መነሳሳትን ፈጥረዋል፡፡ ባለሙያዋ ባካፈሉት የህይወት ታሪክ ውስጥ አንድ ልጅን ከጉዲፈቻ በመውሰድ በአሁኑ ሰዓት እያሳደጉ መሆኑን እና ልጅን በጉዲፈቻ ማሳደግ ከፍተኛ ሰውነታዊና ማህበራዊ ጥቅም ያለው ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ ተግባር ለልጆች የፍቅር ቤተሰብ፣ የተሻለ ኑሮ እና የወደፊት እድል ሲፈጥር፤ ለአዳጊዎችም የአእምሮ ሰላምና ደስታ ያመጣል ብለዋል፡፡

ባለሙያዋ የጉዲፈቻ ልጅ ማሳደግ የወላጅነት ስሜትን በማጠናከር የህይወት ትርጉም እንዲጨምር ያግዛል ለልጁም ፍቅር ድጋፍ እና ደህንነት በማቅረብ ጤናማ ልጅነት እንዲኖረው ያደርጋል በማለት በጉዲፈቻ ልጅን ማሳደግ ሕይወትን የሚቀይርና ሁለቱንም ወገኖች ደስታና ትርጉም የሚሰጥ ልምድ በመሆኑ ይህንን ተግባር አቅሙ የፈቀደ በሙሉ እንዲያደርገው ሀሳባቸውን በማካፈል የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል፡፡