በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በቀረበ ሰነድ ላይ...

image description
image description
image description
image description
- Recent News   

በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
የውይይት ሰነዱን የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞገስ አባተ አቅርበዋል፡፡ የሰነዱ ዓላማ ተብለው ከቀረቡት ውስጥ በየደረጃው ባለው የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመለየት ለመፍታት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገልጋዩ ማህበረሰብ እና የአገልግሎት አቅራቢው ተቋም መብትና ግዴታ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው ባለው የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው እንዲሻሻል በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ የሚሉት ተካተዋል፡፡  በሰነዱ ስለ አገልግሎት ምንነት ፤ ስለ አገልግሎት ባህሪያት ፤ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ ባህሪዎች እና ምቹ ሁኔታ ለአገልግሎት አሰጣጥ በሚሉ ርዕሶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ፡፡ 
በተጨማሪም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሰራተኛው ሚና ምን ይመስላል እና የተገልጋዮች መብትና ግዴታን ጨምሮ በሰፊው የተካተተ ሲሆን ማዕከላችንም ምቹ ሁኔታዎች ተብለው ከተጠቀሱት መካከል የህጻናት ማቆያ፣ የካፍቴሪያ አገልግሎት መስጫ እና የሸማቾች አገልግሎት እንደሚሰጥ በመግለጽ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ በቀጣይ መስተካከል ያለባቸው እና የህዝብን እርካታ ለመጨመር የበለጠ መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ በቀረበው ሰነድ ላይም የተለያዩ ሃሳቦችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳሬክተር እና በማዕዕከሉ የኢኮ ቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ምላሽ በመስጠት የዕለቱን የመወያያ ሰነድ ተጠናቋል፡፡