የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸ...

image description
image description
image description
- Recent News   

የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀረበ

የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የ2018 ዓ.ም የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለማዕከሉ አመራሮች እና አጠቃላይ ሰራተኞች በዛሬው ዕለት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ 
የመክፈቻውን ንግግር የማዕከሉ የኢኮ-ቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ የከፈቱ ሲሆን ሪፖርቱን የማዕከሉ የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ምስክር ታዬ በማዕከሉ መዋቅር ስር የሚገኙ የአራት ዓላማ ፈፃሚ ፤ የሰባት ደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች እና የሁለት ቡድኖችን የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም አቅርበዋል፡፡ 
በቀረበው ሪፖርት ላይ ከቤቱ ለቀረቡት አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡  በመጨረሻም የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም መሻሻል ማሳየቱን እና ማዕከሉ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከዚህ የበለጠ ማደግ እንዳለበት እና በቀጣይ ጥንካሬዎቻችንን የበለጠ አጠናክርን ተቋማችንን ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ ይገባናል በማለት የዕለቱን አጀንዳ ተጠናቋል፡፡