ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ...

image description
image description
image description
- Recent News   

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ አጋራ

የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ለተቸገሩ ወገኖች የፋሲካን በዓልን በማስመልከት ማዕድ አጋራ። በማዕከሉ የሚረዱ አቅመ ደካማ ወገኖች ለፋሲካ በዓል የተዘጋጀላቸውን የማዕድ ማጋራት ስጦታ ከማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ከአቶ ሞገስ አባተ እጅ ተቀብለዋል፡፡ በዚህም ቁጥራቸው አስራ ሁለት ለሚሆኑ በማዕከሉ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ወገኖች ለእያንዳንዳቸው 15 ኪሎ ጤፍ ፣ 3 ሊትር ዘይትና 15 እንቁላል ማዕድ ተጋርቷል ። ድጋፉን የተቀበሉ ወገኖች በተደረገላቸው እገዛ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው የማዕከሉን አጠቃላይ ሰራተኞች አመሰግነዋል።