በወርቃማው ሰኞ አወንታዊ አስተሳሰብ ለስኬት መሠ...

image description
image description
image description
image description
- Recent News   

በወርቃማው ሰኞ አወንታዊ አስተሳሰብ ለስኬት መሠረት ነው ተባለ

የወርቃማ ሰኞ መድረክ የቡድን ስራን በማጠናከር እና ችግሮችን በጋራ በመፍታት የስራ ውጤታማነትን እንዲጨምር ያግዛል በተጨማሪም ሰራተኞችን በማነሳሳት አንድነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው በመጠቆም መድረኩን የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የኢኮቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ አስጀምረዋል፡፡

የዕለቱን የወርቃማ ሰኞ መልዕክት የማዕከሉ ብዝሀ ህይወት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ክፍል (የአካባቢ ትምህርት ግንዛቤ ማስፋፊያ ቡድን መሪ ተወካይ) አቶ እሸቱ ወርቁ አወንታዊ አስተሳሰብ (Positive Thinking) በሚል ርዕስ ዙሪያ ያዘጋጁትን ሰነድ አቅርበዋል፡፡

አወንታዊ አስተሳሰብ በግል ህይወት እና ስራ ቦታችን ላይ ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ችግሮችን እንደ እድል ለማየት ያግዛል፤ ይህም በስራ እና በግል ሕይወት ውጤታማነትን እንዲጨምር እንደሚደርግና አስተሳሰባችንን አወንታዊ ማድረግ ጭንቀትን እንደሚቀንስ እና ግንኙነትን እንደሚያጠነክር በሰፊው አብራርተዋል፡፡ በመጨረሻም ከቤቱ የተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን በመቀበልና ምላሽ በመስጠት የዕለቱ ወርቃማ ሰኞ መድረክ ተጠናቋል፡፡