አወንታዊ አመለካከት ለስራ ስኬት በሚል ርዕስ ሰ...

image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

አወንታዊ አመለካከት ለስራ ስኬት በሚል ርዕስ ሰነድ ቀረበ

የዕለቱን የወርቃማ ሰኞ መድረክ የማዕከሉ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ጌታሁን የከፈቱ ሲሆን አወንታዊ አመለካከት ለስራ ስኬት በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ሰነድ በኢኮቱሪዝም ዳይሬክቶሬት የገበያ ጥናት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ት አሊፋት አስፍር አቅርበዋል፡፡

በሰነዱ ውስጥ አወንታዊ አመለካከት ነገሮችን ሁሉ በደስታ መቀበል ብቻ ሳይሆን በችግሮች ውስጥ ዕድልን በጨለማ ውስጥ ብርሃንን የመፈለግ ጥበብ ነው ብለዋል፡፡

የአወንታዊ አመለካከት ጥቅም ነገሮችን አልችልም ብሎ ከመቀመጥ ይልቅ ምን ማድረግ አለብን ብሎ እንዲያስብ ደርጋል፤ ውድቀትን እንደ ፍጻሜ ሳይሆን እንደ መማሪያ እንድናስበው ያደረጋል፤ ተስፋ እንዳንቆርጥና ለተሻለ ለውጥ እንድንነሳሳ ያደርጋል ፤ በስራ ቦታ ከባልደረቦች ጋር አለመግባባቶችን በጥበብ ለመፍታትና ለውጤታማ የቡድን ስራ የጎላ ጠቀሜታ አለው፡፡

አወንታዊ አመለካከትን ለማዳበር ከአወንታዊ ሰዎች ጋር መገናኘት ምስጋናን ማዘውተር ፤ መልካም ቃላትን መጠቀም እና ትኩረታችንን በማስተካከል አመካከታችንን ማዳበር እንችላለን ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ የሰነዱን አቅራቢ አመስግነው አወንታዊ አስተሳሰብ በተሰማራንበት ሙያ የበለጠ ስኬታማ እንድንሆን ስለሚያስችል ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል