ማዕከሉ ከሌሎች የምርምር ተቋማትና ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚሰሩ ሥራዎችን ማጠናከር አለበት ተባለ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በሚያከናውናቸው የምርምር ሥራዎች ከሌሎች የምርምር ተቋማትና ባለድረሻ አካላት ጋር የሚኖረውን ቅንጅት መጠናከር ይገባዋል ተባለ፡፡ይህ የተገለፀው በማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ በተዘጋጀ እና በርካት የዕፅዋትና ተያያዥ ምርምር ላይ የሚሰሩ ተመራማሪዎች በተሳተፉበት አውደጥናት ላይ ነው፡፡በአውደጥነቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጡ የዘርፉ ሙሁራን በሶስት ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ፁሁፍ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ ስነምህዳርና ጠቀሜታው፣የዕፅዋት ማዕከላት ታሪካዊ ዳራና የሚጫወቱት ሚና እና የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በለፉት ዘስራ አምስት አመታት ምን ሥራዎችን አከናወነ? በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አቅራቢዎቹ ጥናታዊ ፁሁፎች አቅርበዋል፡፡አውደጥናቱን በንግግር መርቀው የከፈቱት የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ናቸው፡