በማዕከሉ የዕፅዋት ስብጥርን በማሻሻል እና የብዝሃ ህይወትን በመንከባከብ ረገድ የተገኘዉ ዉጤት አበረታች መሆኑ ተገለፀ።
ማዕከሉ ባለፉት 9 ወራት ትኩረት ሰጥቶ በሰራቸው ቁልፍ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ሲሆን በተለይም ውጤታማ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራዎችን በማከናወን፣ የዕፅዋት ስብጥርን በማሻሻል እና የብዝሃ ህይወትን በመንከባከብ ረገድ ከፍተኛ ውጤት አሳይቷል።
በመድረኩ የከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ፤የጉለሌ ፅፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡
ማዕከሉ በከተማ ውበት፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በምግብ ዋስትና ዙሪያ ያስመዘገባቸው ውጤቶችና ያጋጠሙትን ፈተናዎች በግምገማ መድረክ ላይ በዝርዝር ቀርበዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በከተማ ግብርና ዘርፍ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ ተጨባጭ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን የችግኞችን የፅድቀት መጠን በማሳደግም የአረንጓዴ መዝናኛ ቦታዎችን በስፋት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።
ከእነዚህ ጎን ለጎንም የመሰረተ ልማት ጥናት፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ዝርጋታ እና የመስኖ መስመር ዝርጋታ ስራዎችን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ መቻሉን አመላክተዋል።
በሌላ በኩል በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ወቅት ከአበረታች ውጤቶች ጎን ለጎን በቀጣይ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሹ ዋና ዋና ጉድለቶች የተለዩ ሲሆን በማዕከሉ ውስጥ የተከሰተው የውሃ እጥረት እና የካፌ አገልግሎት ችግር በአብነት ይጠቀሳሉ።
በዚሁ ግምገማ ላይ ተገኝተዉ የማጠቃለያ ሃሳብ በመስጠት የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ያስቀመጡት የከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ በተለይ ለምርምር የሚዉሉ ዕፅዋትን በመሰብሰብ ላይ፤ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለዉን ትስስር ከማጠናከር አንፃር ፤ለሀገር በቀል ችግኞች ትኩረት ከመስጠት እና ለድጋፍና ክትትል ስራዎች አንፃር ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከከታማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ኮሙኒኬሽን See less
Facebook