የማዕከሉ የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች የወን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

የማዕከሉ የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች የወንዞች ልማት ፕሮጀክት ሥራዎች ላይ ልምድ ቀሰሙ

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የማኔጅመንት አባላትና የሆርቲካልቸር ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ እና በየካ ክፍለ ከተማ መካከል ያከናወናቸውን የወንዝ ልማት ፕሮጀክት ላይ የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

የዕፅዋት ማዕከሉ ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች አንዱ በሆነው የዕፅዋት ጥበቃ ፣እንክብካቤና የማሥዋብ ሥራ ላይ በተለይ በወንዞች ልማት ፕሮጀክት የታየው እጅግ አስደማሚ ከሆነው የአረንጓዴ ልማት ሥራ አፈፃፀም ላይ ማዕከሉ ትልቅ ልምድ ቀስሟል።

ማዕከሉ በቀጣይ በሚያከናውናቸው ተያያዥ ሥራዎች ያገኘውን ልምድ እንደሚጠቀም የሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መክብብ ማሞ ገልጸዋል ።