ቋሚ ኮሚቴው የማዕከሉን የአራተኛ ሩብ ዓመት አፈ...

image description
image description
image description
image description
- Recent News   

ቋሚ ኮሚቴው የማዕከሉን የአራተኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የሚያበረታታ ነው አለ

የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የ2018 ዓ.ም በጀት አመት በአራተኛ ሩብ ዓመት ድጋፍ እና ክትትል እንዲሁም የዕቅድ አፈጻጸም የሚያበረታታ ነው ተባለ ፡፡

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መስክ ላይ በመገኘት የማዕከሉን ሥራዎች ተዘዋውሮ ከተመለከተ በኃላ ከማዕከሉ የማኔጅመንት አባላት ጋር ባደረገው ውይይት አፈፃፀሙ ከባለፉው ዘጠኝ ወራት የተሻለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር አቶሜ አበበ እንዳመለከቱት ኮሚቴው ትኩረት አድርጎ የተመለከታቸው የችግኝ እንክብካቤ፣ የሌብሊንግ፣ የአፈር እና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ዕምርታ ማሳየቱን ፣የሥራ ዕድል ፈጠራ ማደጉን፣ የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር የተሰሩ በርካታ ሥራዎች መኖራቸውን እና የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችም በተወሰነ መልኩ መሻሻል ማሳየታቸው አፈፃፀሙን የሚያበረታታ አድርገውታል ብለዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ትኩረት የሚሹ ስራችዎን ለይቶ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ፣ የኢኮቱሪዝም ሥራዎችን የበለጠ ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል፡፡ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የኢኮቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ እና የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ ቋሚ ኮሚቴው የሰጣቸውን አስተየየትና ምክር ማዕከሉ በቀጣይ ለሚሰራቸው ስራዎች ግብዓት እንደሚሆኑት አመልክተው የማዕከሉን ሥራዎች እና እያጋጠሙት ያሉትን ተግዳሮቶች ለቋሚ ኮሚቴው በሰፊው አስረድተዋል፡፡