"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የጉለሌ ዕፅ...

image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል አመራሮች እና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል አመራሮች እና ሰራተኞች በዛሬው ዕለት የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በድልበር መለስ ፋውንዴሽን አካባቢ 500 ችግኞችን በመትከል የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት ጥረት ውስጥ ጉልህ አሻራቸውን አኑረዋል።
ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል ተከላውን ያስጀመሩት የማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር  አቶ ደበላ ብሩ ሲሆን በንግግራቸው ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በየአመቱ ያለውን የመትከል ባህል በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን እና የከተማዋን አረንጓዴ ሽፋን ለማስፋት፣ አካባቢን ለመጠበቅ እና ለቀጣይ ትውልድ ጤናማ አካባቢ ለማስረከብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡
 በእለቱ በተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የማዕከሉ ሰራተኞች በንቃትና በከፍተኛ የቡድን መንፈስ በመሳተፍ 500 ሀገር በቀል ችግኞች ን ተክለዋል ፡፡