ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በ2018 የዕቅድ አፈጻጸም እና በ2019 ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት እና ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በ2018 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸምን ለመገምገም እና ለ2019 ዓ.ም. የተዘጋጀውን የሥራ ዕቅድ በማቅረብ፣ ከባለድርሻ አካላትና ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞረዳ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መድረኩን ከፍተዋል፡፡
በመቀጠል የማዕከሉ የዕቅድና ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ምስክር ታዬ የማዕከሉን የ2018 ዕቅድ አፈጻጸም በስፋት አቅርበዋል፡፡ በቀረበው ሪፖርት ላይ በማዕከሉ በአላማ ፈጻሚዎች እና በደጋፊ የስራ ሂደቶች የተሰሩ አበይት ስራዎችን የቀረቡ ሲሆን መድረኩን የማእከሉ የበላይ አመራሮች ከባለድርሻ አካላት እና ከማዕከሉ ሰራተኞች በ2018 ዓ.ም. የተከናወኑ ዋና ዋና የሥራ አፈጻጸሞች፣ የተገኙ ስኬቶች፣ የተስተዋሉ ተግዳሮቶች እና ለ2019 ዓ.ም. የተያዙ የማሻሻያ አቅጣጫዎች በስፋት የተወያዩ ሲሆን ተሳታፊዎችም በቀረበው ሪፖርት ላይ ገንቢ አስተያየትና ምክረ ሀሳብ በማቅረብ የተቋሙን አገልግሎት የበለጠ ለማሻሻል የሚያስችሉ ሐሳቦችን አጋርተዋል።
በመጨረሻም ለባለድርሻ አካላት እና የተሻለ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዳይሬክቶሬቶች እንዲሁም ለፈጻሚዎች የምስክር ሰርተፍኬት በመስጠት የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡