በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በመልካም አስተዳደርና አቤቱታ አፈታት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በመልካም አስተዳደር እንዲሁም ቅሬታና አቤቱታ አፈታት ዙሪያ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተካሄደ።
የስልጠናውን መርሃ ግብር በመክፈቻ ንግግር አስጀምረው ያሳለፉት የማዕከሉ አማካሪ አቶ ኑሬ ቀመር ሲሆኑ፣ አግልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና የመልካም አስተዳደር እሴቶችን ማጎልበት ለአንድ ተቋም ውጤታማነት ያለውን ከፍተኛ ሚና አብራርተዋል።
ስልጠናው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት በመጡት የመልካም አስተዳደር ጥናትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ ደምሰው ሽፈራው የተሰጠ ሲሆን፤ በወቅቱም ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ፍትሃዊነትን መሠረት ያደረገ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት መዘርጋት በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም የተገልጋዮችንና የሰራተኞችን ቅሬታ በወቅቱና በብቃት ለመፍታት የሚረዱ የአሰራር ቅደም-ተከተሎች ላይ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አግባብነት ያላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከአሰልጣኙና ከማዕከሉ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።