ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች የጳጉሜን ቀናቶች አስመልክቶ ውይይት አካሄዱ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች የጳጉሜን ቀናቶች አስመልክቶ ውይይት አካሄዱ። የውይይት መድረኩን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞረዳ የመክፈቻ ንግግር አድርገው የከፈቱት ሲሆን፤ ስለ ጳጉሜን ቀናቶች ታሪካዊና ሐገራዊ ፋይዳ የምርምር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደበላ ብሩ ሰፊ ማብራሪያ በዝርዝር አቅርበዋል።
በመድረኩም የጳጉሜን ቀናቶች እያንዳንዱን መንፈስ እና መርህ የሚገልጹት ጳጉሜን 1 የዕምርታ፣ ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን፣ ጳጉሜን 3 የጽናት ቀን፣ ጳጉሜን 4 የህብር ቀን እንዲሁም ጳጉሜን 5 የነገ ቀን በመሆን በውይይቱ ላይ በዝርዝር ተነስተውበታል። በስተመጨረሻም በቀረቡት ሃሳቦች ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳቦች ቀርበው ውይይቱ ተጠናቋል