ጳጉሜን 3 የጽናት ቀን በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮች እና አጠቃላይ ሰራተኛው በተገኘበት የጳጉሜን 3 የጽናት ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶችና መርሃ ግብሮች አክብሯል።
ከዝግጅቶቹ መካከልም በዕለቱ ፅናትን የሚያንጸባርቁ ግጥሞች ፣ ፅናትን ትርጉምና የትዕግሥት እሴት የሚያስተላልፍ ድራማ እንዲሁም የፓናል ውይይት ቀርቦ ለሰራተኞች መልዕክት አስተላልፏል።
በመጨረሻም የዕለቱ ዝግጅት በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በአንድነት በመዘመር ተጠናቋል።