ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ከአ...

image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ከአሥሩም ወረዳዎች ለተውጣጡ አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋራ

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ጳጉሜ 4 ቀን የህብር ቀንን አስመልክቶ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ከአሥሩም ወረዳዎች ለተውጣጡ 100 አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አከናወነ።

የበዓል እና የመተሳሰብ ቀናትን ከኅብረተሰቡ የተቸገሩ ክፍሎች ጋር በጋራ ለመካፈል ታስቦ የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር፤ የዕፅዋት ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ለተጋባዦች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልእክት በይፋ ተጀምሯል።

ዋና ዳይሬክተሩ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ተቋሙ ከተፈጥሮ ጥበቃ እና ቱሪዝም ስራዎቹ ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እና ህብረተሰቡን በዘላቂነት ለመደገፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። በመርሃ ግብሩ ላይ ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ አቅመ ደካሞች የተገኙ ሲሆን፣ ለዕለቱ የተዘጋጀውን ልዩ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም የተገኙት የበጎ አድራጎት ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየት ለተደረገላቸው ድጋፍ የበዓሉን ቀናት በደስታ እንዲያሳልፉ ትልቅ እገዛ እንዳደረገላቸው ገልጸው ለተቋሙ የስራ ኃላፊዎች እና ለተባባሪ አካላት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።