23ኛው የፀረ-ሙስና ቀን በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ተከበረ።
የዕለቱን መርሐ ግብር የዕፅዋት ምርምርና ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ በማስጀመር፣ የፀረ-ሙስና ትግሉን ማጠናከርና የሥነ-ምግባር አሠራርን ማስፋፋት የሚጠይቀውን የተቋማት ሚና አስመልክተው መድረኩን አስጀምረዋል።
በመቀጠል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኤሊያስ ከበደ በፀረ-ሙስና እና በሥነ-ምግባር ዙሪያ የተዘጋጀውን ሰነድ በማቅረብ ለተሳታፊዎች ግንዛቤ ሰጥተዋል።
በሰነዱ ውይይት ወቅትም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን፣ ለተነሱት ጥያቄዎችም ሙያዊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል። ይህም ተሳታፊዎች በፀረ-ሙስና አሠራር፣ በሥነ-ምግባርና በተቋማዊ ታማኝነት ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያጎለብቱ አስተዋፅኦ አድርጓል