ተፈጥሮ ሸራችን፣ ቀለም ቋንቋችን” የስዕል ኤግዚ...

image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

ተፈጥሮ ሸራችን፣ ቀለም ቋንቋችን” የስዕል ኤግዚቢሽን በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተከፈተ

ተፈጥሮን በሥነ-ጥበብ አማካኝነት የሚያስተዋውቀውና የተፈጥሮን ውበት በተለየ የእይታ አቅጣጫ እንዲዳሰስ ዕድል የሚፈጥረው “ተፈጥሮ ሸራችን፣ ቀለም ቋንቋችን” የስዕል ኤግዚቢሽን በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተከፈተ።

ኤግዚቢሽኑ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል እና በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በማዕከሉ አጎራ ሁለት አዳራሽ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የምርምርና ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ እና በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የኪነ-ጥበብ ሀብቶች ልማት የሥርፅት ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ደኑ በይፋ ተከፍቷል።

በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተሳተፉት ሰዓሊያንም የሥዕል ሥራዎቻቸውን ለታዳሚያን በማቅረብ፣ በሥዕሎቹ ውስጥ የተንጸባረቁትን ሐሳቦች፣ መልዕክቶችና የፈጠራ ሂደቶች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ይህም ታዳሚያን የተፈጥሮን ውበት በሰዓሊያኑ የፈጠራ ዓይን እንዲመለከቱና ከሥዕሎቹ ጀርባ ያሉትን መልዕክቶች በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ ዕድል ፈጥሯል።

የስዕል ኤግዚቢሽኑ እስከ ሕዳር 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 12 ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ ጎብኚዎች በማዕከሉ በመገኘት የሥነ-ጥበብና የተፈጥሮ ውበትን በአንድ ላይ እንዲያጣጥሙ ጥሪ ቀርቧል።