የሥራ ትብብር ለማድረግ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ...

image description
- Events Recent News    0

የሥራ ትብብር ለማድረግ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልና በኢትዮጲያ የዱር እንስሳት ሕክምና አገልግሎት መካከል የሥራ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡የጋራ መግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ውስጥ የሚገኙትን የዱር እንስሳት ጤና ከበሽታ ለመጠበቅ እና ለመቆጣጠር እንዲሁም በሰውና በዱር እንስሳት አኗኗር ላይ የሚከሰትን ተቃርኖ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት በሚሉትና በመሳሰሉት ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለመስራት እንደሆነ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጲያ የዱር እንስሳት ሕክምና አገልግሎት በኩል በሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር የሆኑት ጆርጅ ፍራንሲስ ላውረስ ሲሆኑ በማዕከሉ በኩል ደግሞ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ናቸው፡፡

ከፊርማ ስነ-ስርዓቱ ቀደም ብሎ የሕክምና አገልግሎት ተቋሙ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የሰራቸውን በርካታ ሥራዎች አስመልክተው ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሩ ገለጻ አድርገዋል፡፡ በመጨረሻም የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ ለማዕከሉ እጅግ ጠቃሚ የሆነ ሙያዊ እገዛ ለማድረግ የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈረም ላሳየው ቁርጠኝነት በራሳቸውና በማዕከሉ ስም ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ማዕከሉ ቀደም ብሎ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የነበረው በዕፅዋት ጥበቃና እንክብካቤ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፈጠረ በሚገኘው ምቹ ሁኔታ በርካታ የዱር እንስሳት ማዕከሉን መኖሪያቸው እያደረጉት በመሆኑ ከዕፅዋት እንክብካቤው ጎን ለጎን የዱር እንስሳቱን ጤና የመጠበቅ፤ የመቆጣጠርና ከሰው ጋር የሚኖራቸውን መስተጋብር ከተቃርኖ ነጻ እንዲሆን የማድረግ ሥራ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በጋራ መስራቱ የማይተካ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የማዕከሉ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments