
የዓለም አካባቢ ቀንን አስመልክቶ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የእግር ጉዞ ተካሄደ
በአለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ግንቦት 28 ቀን የሚከበረውን የአለም የአካባቢ ቀንን አስመልክቶ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የእግር ጉዞ ተካሄደ፡፡በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንና በአደስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁም ቁም ለኢትዮጵያ የሚባል የአካባቢ ተቆርቋሪ ማህበር በጋራ ፕግራሙን እንዳዘጋጁት ተገልፃል፡፡በዝግጅቱ ማስጀመሪያ ላይ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የኢኮቱሪዝምና ፕሮሞሽን ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አማረ የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የዕፅዋት ማዕከሉ አሁን የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ያከናወናቸውን የልማት ሥራዎች በማብራራት የአለም የአካባቢ ቀን ሲከበር ከያዛቸው መልዕክቶች መካከል በተለይ የመሬት ማገገም የሚለው ለጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል፡፡ በመቀጠል ፕግራሙን በይፋ ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር የአካባቢጥበቃ ባለስልጣንዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ51ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ31ኛ ጊዜ “የመሬት ማገገምን፣በረሀማነትንና ድርቅን መቋቋም (Land Restoration,Desertification and Drought Resilience)“ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ መሆንን ገልፀው ዜጎች ለአካባቢያቸው መጠበቅ በባለቤትነት ስሜት ሊሰሩ ይገባል በማለት የእግር ጉዞውን አስጀምረዋል፡፡የእግር ጉዞው መዳረሻ በሆነው የደቡብ በር አካባቢ ባለፈው ዓመት የተተከሉ ችግኞችን ውሀ በማጠጣት ዝግጅቱ ተፈፅሟል፡፡በፕሮግረሙ ላይ የጀነራል ታደሰ ብሩና የበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም ተሳትፈዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments