“ተፈጥሮ ለቱሪዝም ያለው ፋይዳ እና ተግዳሮቶች...

image description
- Events Recent News    0

“ተፈጥሮ ለቱሪዝም ያለው ፋይዳ እና ተግዳሮቶች “ በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተካሄደ

በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል እና በአዲስ ሚዲያኔትወርክ ትብብር አዘጋጅነት “ተፈጥሮ ለቱሪዝም ያለው ፋይዳ እና ተግዳሮቶች “ በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተደረገ፡፡የፓናል ውይይቱን በእንኳን ደህና መጣቹ የመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞረዳ ሲሆኑ ተሳታፊ እንግዶችን እንኳን በደህን መጣቹ ካሉ በኃላ የፓናል ውይይቱ በተለይ የኢኮቱሪዝም አገልግሎትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የተገልጋዩን የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ ለማሳደግ ይጠቅማል ብለዋል፡፡ለፓናል ውይይቱ መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ፅሁፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝም ዲቭሎፕምንት መምህር በሆኑት ዶ/ር ኤፍሬም አሰፋ ቀርቦ በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በዚህም የዕፅዋት ማዕከሉ እየሰጠ የሚገኘውን ከተፈጥሮ ጋር የተስማማ የኢኮቱሪዝም አገልግሎት በቀጣይ የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እንዲያሰችለው በርካታ አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተሰጥተዋል ፡፡ በተሠጡት አስተያይቶችና ጥያቄዎች ላይ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ማብራሪያ ስጥተዋል፡፡በመጨረሻም ቀደም ሲል ህዳር 27/2017 ዓ.ም በነበረ መድረክ የማዕከሉ ማኔጅመንት የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የክብር አምባሳደር አድርጎ የሾመው ታዋቂው ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የክብር ሰርተፊኬቱን በፓናል ውይይቱ ላይ ከታደሙት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስተር ደኤታ ከአቶ ስለሺ ግርማ እጅ ተቀብሏል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments