
በሥነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት እና በአደስ አበባ ከተማ ሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ትብብር የተዘጋጀ የስነምግባር ስለጠና ለማዕከሉ አጠቃላይ ሠራተኞች ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሠጡት በኮሚሽኑ ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ የሆነት አቶ አቤል ሳኩሜ ሲሆኑ የሥነ-ምግባር ምንነት፣የስነምግባር ንድፈ ሀሳቦችና ምንጮች፣ስነምግባር ላይ ማትኮር ለምን እንዳስፈለገ ፣ የሥነምግባር ጉድለት የሚያስከትላቸው ጉዳቶች እና የስራ ሥነምግባር በሚሉት ርዕሶች ላይ በሰነድ የተደገፈ ሰፊ ማባራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከተሳታፊ ሠራተኞች ከማዕከሉ የሥራ ተፈጥሮ ጋር በማያያዝ በተነሱት ርዕሰ ጉዳች ላይ ጥያቄና አስተያየቶችን በማንሳት ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡በመጨረሻም በኮሚሽኑ የተደረገ የሀብት ምዝገባ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለሠራተኛው ተሰጥቷል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments