
የመሬት እና የግንባታ ጉዳች ቋሚ ኮሚቴ የዕፅዋት ማዕከሉን ሥራዎች ተዘዋውሮ ጎበኘ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬት እና የግንባታ ጉዳች ቋሚ ኮሚቴ የዕፅዋት ማዕከሉን ሥራዎች ተዘዋውሮ ጎበኘ፡፡በቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተመራው ኮሚቴው የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል እያከናወነ የሚገኙትን የፕሮጀክትና የመደበኛ ሥራዎች የሚገኙበትን ደረጃ የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ችግሮችን በሰፊው በመዘዋወር ከጎበኙ በኃላ የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸዋል፡፡የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ጃራ ሰማ እና አባላቱ የዕፅዋት ማዕከሉ ያለበት የአፈፃፀም ቁመና ጥሩ መሆኑን ገልፀው ላቀረቡት እስተያየትና ጥያቄ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ እና ሌሎች አመራሮች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments