የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የጉለሌ የዕፅዋት ማዕ...

image description
- Events Recent News    0

የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን ጎበኙ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙት ከአስራአንዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎቹ ቡድን በዕፅዋት ማዕከሉ በተገኘበት ወቅት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ተቀብለው እንኳን ደህና መጣቹ ካሉ በኃላ የዕፅዋት ማዕከሉ የአዲስ አበባ ከተማን የአየር ፀባይ ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የማይተካ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ የዕፅዋት ማዕከሉ የሀገራችንን የዕፅዋት ዝርያ የሚጠብቅና ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሆነ አመልክተው የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎቹም ሥራዎቹንና የዕፅዋት ልማቱን ተዘዋውረው በመጎብኘት በማህበራዊ ሚዲዎቸቸው በማስተዋወቅ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

የጉለሌየዕፅዋት ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ የዕፅዋት ማዕከሉ የተቋቋመበትን ዋና ዋና አላማዎች ላይ ገለፃ ካደረጉ በኃላ የአላማ ፈፃሚ ዳይሬክቶሬቶች ኃላፊዎች ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡

የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎቹ የዕፅዋት ማዕከሉን ልዩ ልዩ ክፍሎችና መልካምድራዊ አቀማመጥ ተዘዋውረው ከጎበኙ በኃላ በሰጡት አስተያይት ማዕከሉ እያከናወናቸው ባለው የዕፅዋት ልማትና እንክብካቤ እንዲሁም እየተገነቡ በሚገኙት ፕሮጀክቶች በእጅጉ መደሰታቸውን ገልፀው ማዕከሉን ለህብረተሰቡ በማስተዋቅ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments