በህንፃ አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተጠናቀቀ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የህንፃ አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክቶሬት በህንፃ አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ያዘጋጀው የግንዛቤ መድረክ ተጠናቀቀ፡፡የህንፃ አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሚኪያስ ሀበቱ የህንፃ መመሪያ ቁጥር 1/2013 ምን ምን ነገሮችን እንዳከተተ እና መመሪያውን ተሞርክዞ መሠራት ያለባቸው ስራዎች ምንድን ናቸው? በሚሉትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በመድረኩ ሠራተኛውን በሰፊው ግንዛቤ ማስጨበጥ ተቻሏል ብለዋል፡፡ይህ ደግሞ በቀጣይ በሥራ ላይ የተሻለ ግልፅነትን፣ኃላፊነትና ግዴታን በአግባቡ ለመወጣት እንዲሁም አላስፈላጊ የተግባር ድግግሞሽን ይቀንሳል ሲሉ አቶ ሚኪያስ ገልፀዋል፡፡ ለስምንት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው በዚህ የግንዛቤ ማሳጨበጫ መድረክ አንድ መቶ ሰማኒያአንድ(181) ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡