የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች አ...

image description
- Recent News   

የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዶ አሻራቸውን አኖሩ

በሀገር ደረጃ ለሰባተኛ ጊዜ እየተካሄደ ባለው የ2017 ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መረሀ-ግብር የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኖሩ፡፡በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ለሰባተኛ ጊዜ እየተካሄ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ችግኝ የሚንተክለው ባለፉት ስድስት ዓመታት የተተከሉት ችግኞች ያመጡትን ተጨባጭ ለውጥ ከግምት በማስገባት መሆን አለበት ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ የዕፅዋት ማዕከሉ በከተማችን ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ በማቅረብ የድርሻውን እየተወጣ እንደሆን ገልፀው የማዕከሉ ሠራተኞች የሚተክሏቸውን ችግኞች እንደ ቀደመው ጊዜ እንዲንከባከቡ አሳስበዋል፡፡ማዕከሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ከተጀመረ ጀምሮ በየአመቱ ሀምሳ ሺ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ ላይ ይገኛል፡፡