የስደተኞች እና ተመላሾች ድርጅት ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
የስደተኞች እና ተመላሾች ድርጅት ሠራተኞች ዛሬ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ፡፡የድረጅቱ ሠራተኞች ልዩ ስፍራው ቃሌ በመባል በሚታወቀው የማዕከሉ ክፍል በተከታታይ በየዓመቱ አረንጓዴ አሻራቸውን በማሳረፍ የድርሻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡በዛሬው ዕለትም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት በቦታው በመገኝት ሁለት ሺ(2,000)ችግኞችን በመትከል አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡የድርጅቱ ሠራተኞች የተከሏቸው የአፕል፣የአቡካዶ፣የወይራ ፣የዝግባና የኮሶ ችግኞች ናቸው፡፡