''በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ'' በሚል መሪ ቃል የበጎ አድራጎት ሥራ ተጀመረ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ከጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ጋር በተደረገ ስምምነት የበጎ አድራጎት ሥራ ተጀምሯል ። በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የበጎ ፈቃድ ሥራ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አጋር በሆነው በፍሊንስቶን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ የአንድ እናትን የተጎሳቆለ ቤት አፍርሶ ደረጃውን የጠበቀ ቤት የመስራት ሂደት ተጀምሯል ።
እጅግ የተጎሳቆለውንና ለኑሮ ምቹ ያልሆነውን አሮጌ ቤት በማፍረስ ሰሥራውን ያስጀመሩት የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማሞሮዳ እና የወረዳው ወና ስራ አስፈፃሚ እመቤት ፍቃዱ እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ናቸው።ቤቱን መልሶ ግንብቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ የኮንስትራክሽን ካምፓኒው ተወካይ የገለፁ ሲሆን ማዕከሉ ካምፓኒው ካለፋት አመታት ጀምሮ ላደረገው ድጋፍ የዕውቅና ሰርተፊኬት አበርክቶለታል ።