ማዕከሉ በአረንጓዴ ልማት ላይ ለተደራጁ ወጣቶች እና ሴቶች ስልጠና መስጠት ጀመረ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በአረንጓዴ ማስዋብ ሥራ ላይ በማህበር ለተደራጁ ወጣቶችና ሴቶች የአምስት ቀናት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በመክፈቻ ስንስርዓቱ ላይ የተገኙት የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ ስልጣኞቹን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ ስልጠናው ለተሰማሩበት ዘርፍ ተጨማሪ አቅም ስለሚሆናቸው በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡ስልጠናውን ያዘጋጀውና ያስተባበረው የማዕከሉ የብዝሀህይወት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ሲሆን ከሌሎች የሥራ ክፍሎችም የተውጣጡ ባለሙያዎች በአሰልጣኝነት ይሳተፋሉ፡፡ ስልጠናው የሚሰጠው የዕፅዋት እንክብካቤና ስለዕፅዋት አገራረዝ፣የዕፅዋት የማባዛት ሂደት፣የኮምፖስት ዝግጅት እና በመሬት አጠቃቀም ዙሪያ መሆኑ ታውቋል፡፡