የማዕከሉ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም አበረታች እንደሆነ ተገለፀ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም አበረታች መሆኑን የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሬትና ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ፡፡የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በዚህም በምርምር ፣ በብዝሀህይወት ትምህርት ፣ በሆርቲካልቸር ልማት፣በኢኮቱሪዝም ዘርፎች የተከናወኑትን ሥራዎች በሰፊው ያቀረቡ ሲሆን ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተፈቱበትን አግባብም አመላክተዋል፡፡ቋሚ ኮሚቴው ሪፖርቱን ካዳመጠ በኃላ ተጨማሪ ሰነዶችንና መረጃዎችን በስፋት የተመለከተ ሲሆን በማዕከሉ እየተከናወኑ የሚገኙትን ሥራዎች በመስክ በመዘዋወር ጎብኝቷል፡፡በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው አባላት ማዕከሉ በዝግጅት ምዕራፍ ለማከናወን ያቀዳቸውን ሥራዎች የፈፀመበት መንገድ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀው ለማዕከሉ የሚያደርጉትን ክትትልና ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡