በአፈፃፀም አመራር ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የመካከለኛ አመራሮች በአፈፃፀም አመራር(performance management ) ዙሪያ ስልጠና እየወሰዱ ነው። ስልጠናው በአዲስ አበባ ሥራ አመራር ኢኒስቲቲዩት እየተሰጠ ሲሆን ቁጥራቸው 23 የሚሆኑ የማዕከሉ የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች እና የቡድን መሪዎች ስልጠናውን እየተካፈሉ ይገኛሉ ።ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሠጥ ታውቋል።