የማዕከሉ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለአጠቃላይ ሰራተኛው ቀረበ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ለማዕከሉ አጠቃላይ ሰራተኞች ቀርቦ ውይይት ተካሄደበት ፡፡ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀም የሚያበረታታ ቢሆንም ሠራተኛው ቀረ የሚላቸውን፣ ያጋጠሙ ፈተናዎችንና የነበሩ ዕድሎችን በዝርዝር ተወያይቶባቸው ለቀጣይ ሥራዎቻችን ግብዓት እንዲሆኑ ማድረግ ይገባዋል ብለዋል፡፡ ሪፖርቱ የአራቱን ዓላማ ፈፃሚ ማለትም የምርምር ፣ የብዝሀህይወት ትምህርት ፣ የሆርቲካልቸር ልማት፣የኢኮቱሪዝም ዘርፎችና የደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች የዕቅድ አፈፃፀምን በሰፊው ዳስሷል፡፡ከሪፖርቱ በኃላ በተደረገ ውይይት የየስራ ክፍሎቹ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች በተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ውይይቱን የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ እና የማዕከሉ አማካሪ አቶ ፋሩቅ ጀማል መርተውታል፡፡በመሆኑም ስለ አጠቃላይ የሠራተኛው የሥራ ስምሪትና ቁጥጥር፣ በአንዳንድ የሥራ ክፍሎች የሚታዩ የሚና መደበላለቅ ፣ የንብረት አጠባበቅና አገልግሎት ላይ ማዋል፣ማዕከሉን በሰፈው ከማስተዋወቅ አንፃር እና በሌሎችም በውይይቱ በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ዝርዝር አቅጣጮ በመስቀመጥ አወያዮቹ መድረኩን አጠቃለዋል።