ወርቃማው ሰኞ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተካሄደ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በወርቃማው ሰኞ ወርቃማ ልምዶችን በማካፈል ሳምንቱን በአዲስ መንፈስ እና በተነቃቃ መልኩ የተሰጠንን ኃላፊነት እንዴት መወጣት እንዳለብን በሚያሳይ ስኬት በሚል ርዕስ በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
የዕለቱን አጀንዳ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኢንጂነር ጉተማ ሞረዳ የከፈቱት ሲሆን በወርቃማው ሰኞ ሰራተኛው ከህይወት ተሞክሮ ፣ ከስራ ልምድ እና ከትምህርት የሚያገኘውን አስተማሪና አዝናኝ የሆኑ ልምዶችን ማካፈል ለተሻለ ስራ እንደሚያግዝ በመግለጽ ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡
በመቀጠል የማዕከሉ አማካሪ በሆኑት አቶ ፋሩቅ ጀማል ”ስኬት” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ሰነድ ውስጥ ስኬት ማለት ምን ማለት ነው፤ አንድ ሰው ስኬታማ እንዲሆን የሚያስፈልጉት መሰረታዊ ብቃቶች ፤ የስኬት መርሆች፤ የስኬት ቁልፎች እና ስኬታማ እንዳንሆን ወደ ውድቀት የሚወስዱንን አቅጣጫዎች የሚያመለክት አስተማሪ ሰነድ ቀርቦ በማዕከሉ ሰራተኞች ውይይት ተደርጎበታል፡፡