የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግበረ መልስና የጥቅምት ወር አፈፃፀም በዘርፍ እየተገመገመ ነው
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግብረመልስ እና የጥቅምት ወር አፈፃፀም ግምገማ አያካሄደ ነው፡፡ በተለይ የኮሙኒኬሽን፣ የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ፣ የመንግስት ግዢ እና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬቶች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ዘርፉን የሚመሩት የማዕከሉ አማካሪ አቶ ፋሩቅ ጀማል ከዕቅድ በላይ ወይም በታች ለተሰሩ ሥራዎች ምክንያታቸውን ዳይሬክቶሬቶች እንዲያስቀምጡ ካደረጉ በኋላ በቀጣይም እንዲስተካከሉ ባሉባቸው ሥራዎች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡