በማዕከሉ ብራንድ አምባሳደር የተመራው ቡድን ማዕከሉን ተዘዋውሮ ጎበኘ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ኮሙኒኬሽን
በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ብራንድ አምባሳደር በተጓዥ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የተመራ የታዋቂ ሰዎች ቡድን ማዕከሉን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።ታዋቂውን የሙዚቃ ባለሙያ ሰርፀ ፍሬሰንበትን እና ሌሎች በተለያዩ ሙያዎች አንቱ የተባሉ ሙሁራንን ቡድኑ አካቷል።የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ ቡድኑን ተቀብለው በማዕከሉ እየተከናወኑ ያሉትን ሥራዎች እና የተፈጥሮ ፀጋዎች አሰግብኝተዋል።የቡድኑ አባላት ባዩት ነገር በእጅጉ መደመማቸውን ገልፀው በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ማዕከሉን እንደሚያስተዋውቁ ገልፀዋል ።