ወርቃማው ሰኞ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተካሄደ

image description
- Recent News   

ወርቃማው ሰኞ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተካሄደ

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በወርቃማው ሰኞ ወርቃማ የሆኑ የሥራ ላይ ፣ የትምህርት ላይ እና የህይወት ተሞክሮዎችን የሚያካፍልበት መድረክ ነው፡፡ 

የዛሬውን የወርቃማ ሰኞ የህይወት ተሞክሮ እርስ በእርስ የምንማማርበት እና ጠቀሜታውም ላቅ ያለ መሆኑን በመግለጽ መድረኩን  የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞገስ አባተ አስጀምረዋል፡፡  

በመቀጠል የዕለቱን መልዕክት የማዕከሉ የሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መክብብ ማሞ ”አወንታዊ አመለካከትን መገንባት” (Build Positive Attitude) በሚል ርዕስ ላይ ተመርኩዘው አመለካከታችንን በቤተሰብ ውስጥ በስራ ቦታ እና በግል ሕይወታችን እንዴት አዎንታዊ ማድረግ እንችላለን በሚሉ ነጥቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ 

በመጨረሻም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ጌታሁን በዕለቱ በቀረበው ርዕስ ዙሪያ እንዲወያዩ በማደረግ የዕለቱን መድረክ አጠቃለዋል፡፡