ለማዕከሉ የጥበቃ ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ቁጥራቸው ከ150 በላይ ለሆኑ የማዕከሉ ቋሚና ጊዜያዊ የጥበቃ ሰራተኞች በማዕከሉ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
የቱሪዝም ልማትና ፕሮሞሽን ዳ/ት የእንግዳ ቅበላ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አበበ ስንታያሁ እንደገለጹት ስልጠናውን ከወረዳ 8 የመጡ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት እየሰጡ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ከስልጠናው የሚገኘውን ጠቀሜታ በተመለከተ ማዕከሉን በሰለጠነ የሰው ሀይል ለማስጠበቅ ፣ ወንጀልን በበቂ ሁኔታ በመከላከል ማዕከሉን ለጎብኚዎች ከስጋት ነፃ ለማድረግ የጥበቃውን ክፍል ለማነቃቃት ተብሎ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ስልጠናው ለሚቀጥሉት 12 ቀናት እንደሚቆይ ተናግረዋል፡፡