የህይወት ተሞክሮ የተካፈለበት ወርቃማው ሰኞ ተካ...

image description
- Recent News   

የህይወት ተሞክሮ የተካፈለበት ወርቃማው ሰኞ ተካሄደ

የህይወት ተሞክሮ የተካፈለበት ወርቃማ ሰኞ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተካሄደ፡፡የማዕከሉ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ገ/ህይወት የህይወት ተሞክሯቸውን ለማዕከሉ ሰራተኞች አጋርተዋል፡፡በዚህም በ17 ዓመት የመንግስት ሥራ  የአገልግሎት ዘመናቸው በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ማገልገላቸውን ጠቅሰው በርካታ ፈተናዎችን በትዕግስትና በብልሀት ማለፋቸውን አጋጣሚዎቹን በአብነት እያስደገፉ አብራርተዋል፡፡በተለይ አቶ ሀብታሙ ከተምህርት ወደ ሥራ አለም ሲገቡ በሚሰሩበት ወረዳ የነበረው ቢሮክራሲ ሙያቸው ላይ በአሉታዊ መልኩ ከፍተኛ ተፅኖ ፈጥሮባቸው እንደነበረ ገለፀዋል፡፡ነገር ግን በነበራቸው የአላማ  ፅናትና  ለሙያቸው ይሰጡት በነበረው የሙያ ክብር ፈተናዎችን ተጋፍጠው እንዳለፉ ገልፀው የማዕከሉም ባልዳረቦቻቸው በሥራ ላይ የሚገጥማቸውን ፈተና በፅናት በመታገል በሙያቸው የሚጠበቅባቸውን ውጤት ለማምጣት መጣር እንዳለባቸው ከልምዳቸው አካፍለዋል፡፡