የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የክትትልና ድጋፍ ሪፖርት ቀረበ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የተደረገ የክትትልና ድጋፍ ሪፖርት ቀረበ፡፡
የማዕከሉ ጠቅላላ ካውንስል አባላት በተገኙበት ሪፖርቱ የቀረበ ሲሆን በሩብ ዓመቱ በተሰሩ ስራዎች የነበሩ ጥንካሬዎች እና ክፍተቶች ተነስተዋል፡፡
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ የክትትልና ድጋፍ ኮሚቴው ያቀረበውን ሪፖርት በሩብ ዓመቱ በዕቅድ ተይዘው የተከናወኑና ያልተከናወኑ ስራዎቸን ያሳየ በመሆኑ በቀጣይ የዕርምት እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል ብለዋል፡፡ የካውንስል አባላቱ ሪፖርቱ ላይ በሰፊው ከተወያዩ በኋላ የጋራ በማድረግ ተጠናቋል፡፡