ወርቃማው ሰኞ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል
ወርቃማው ሰኞ በማዕከሉ የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ሰራተኞችን ሊያስተምር ይችላል ተብለው በተመረጡ ርዕሶች ላይ ልምዶችን የሚለዋወጥበት መድረክ ነው፡፡
የዛሬው የወርቃማ ቀን ርዕስ ”ለሀገር ብልጽግና መትጋት” የሚል ሲሆን ሰነዱን የማዕከሉ አማካሪ የሆኑት አቶ ፋሩቅ ጀማል አቅርበዋል፡፡
በሰነዱ ውስጥ ሀገራዊ የሆኑ እና ወደ ግል ህይወት እና ወደ ሥራ ቦታችን አምጥተን ልንተገብራቸው የሚገቡ ሃሳቦች ተካተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ጊዜና ጉልበትን ሌሎችን ለመርዳት መጠቀም ፣ ህግና ስርዓትን ማከበር አካባቢን መንከባከብ ፣ መልካም ሃሳቦችን በነፃነት መግለጽ፣ ከተሰጠን ሃላፊነት በላይ መስራት፣ የሀገራችንን ታሪክ ጠንቅቀን ማወቅ ፣ ከመብት በፊት ግዴታችንን መወጣት እንዳለብን፤ የተለያዩ በጎ አድራጎት ስራ ላይ መሳተፍ ፤ እና የሀገር ፍቅር ሊኖረን እንደሚገባ ከሰነዱ እና ከህይወትና ከስራ ላይ ተሞክሯቸው ጭምር በማጣቀስ አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ኑሬ ቀመር (የማዕከሉ አማካሪ) ሀገር ማለት ህይወት ማለት እንደሆነ እና የሀገርን ጠቀሜታ በጦርነት ምክንያት ችግር ውስጥ ከወደቁት ጎረቤት ሀገሮች መማር እንደምንችል በመግለጽ ሀገራችንን በየትኛውም መልኩ በተሰማራንበት የሙያ ዘርፍ በትጋት በመስራት የተጀመረውን ለውጥ ዳር ማድረስ እንዳለብን መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የዕለቱን መድረክ ተጠናቋል፡፡