የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ሰራተኞች ዲሞክራሲ እና...

image description
image description
image description
image description
- Recent News   

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ሰራተኞች ዲሞክራሲ እና የፌደራል ስርዓት በኢትዮጲያ ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶች በሚል መወያያ ሰነድ ላይ ተወያዩ

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደሬሽን ም/ቤትና ከአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጋር በመቀናጀት ለ20ኛው የኢትዮጲያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የተዘጋጀ መወያያ ሰነድ ላድ ውይይት አደረጉ፡፡

የማዕከሉ አማካሪ የሆኑት አቶ ፋሩቅ ጀማል የኢትዮጲያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድነትና የሐይማኖት እኩልነት በመተግበር በአንድነት በምናከብርበትና የህዝቦችን ባህል በኩራት የማስተዋወቅ እድልን የሚፈጥር እና የእርስ በእርስ ትስስር የሚያጠናክር መልካም አጋጣሚ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባን በመግለጽ የዕለቱን አጀንዳ አስጀምረዋል፡፡

የመወያያ አጀንዳውን በማዕከሉ ውስጥ የብዝሀ ሕይወት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዩሀንስ መላኩ ያቀረቡ ሲሆን ሰነዱ በዋናነት በዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ ላይ ያተኮረና ዲሞክራሲ ማለት ሁሉንም የሚያሳትፍ ስርዓት መሆኑን እና በተጨባጭ የሚያስገኘውን ውጤት በሰፊው በመግለጽ ዲሞክራሲ የሌላቸው ሀገሮች ግጭቶችን በመግባባትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተግዳሮት እንደሚሆንባቸው በሰነዱ ተካቷል፡፡

በመቀጠል የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞገስ አባተ ከቀረበው ሰነድ በመነሳት ዲሞክራሲና ብሄር ብሄረሰብን አስመልክተው በሀገራችን ኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ ብሄርብሄረሰቦች የራሳቸው ባህልና ወግ ያላቸው እንደመሆኑ ሁሉም ብሄርብሄረሰብ ያለምንም አድሎ በእኩልነት ማግኘት የሚገባውን መብት ለማግኘት የቻለው ሀገራችን የዲሞክራሲ ስርዓትን የምተከተል ሀገር በመሆኗ ነው ብለዋል፡፡

በሰነዱ በስፋት በተነሱት ርዕሶች ላይ ማለትም ስለ ዲሞክራሲ ምንነትና ዲሞክራሲ ለአንድ ሀገር ያለውን ጠቀሜታ እንዲሁም በፌደሬሽን እና በፌደራሊዝም መካከል ስላለው አንድነት እና ልዩነት ሰራተኛው እንዲወያይባቸው ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም የማዕከሉ የምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ዲሞክራሲ በሀገራችን በተለያዩ ዘመናት በተለያየ መንገድ ሲተገበር የነበረ ቢሆንም አሁን ካለው ስርዓት ጋር ሲነጻጸር አሁን ዜጎች መብታቸውን በግልጽ የሚገልጹበት፤ ባህላቸውን ወጋቸውን በመከባበር ጠብቀው ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሀሳባቸውን የሚገልጹበትም ጭምር ነው በማለት የዕለቱን የመወያያ አጀንዳ ተጠናቋል፡፡