በወርቃማ ሰኞ መልካም ስነምግባርን በመላበስ ሙ...

image description
image description
- Recent News   

በወርቃማ ሰኞ መልካም ስነምግባርን በመላበስ ሙስናን መዋጋት እንደሚገባ ተገለፀ

የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ጠቅላላ ሰራተኞች በታደሙበት የዛሬው የወርቃማ ሰኞ ፕሮግራም ላይ በቀረበ ሰነድ መልካም ስነምግባርን በመላበስ ሙስናን መከላከል እንደሚገባ ተገልፀ  ፡፡ የማዕከሉ የስነምግባርና የፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ከበደ ሰነዱን አቅርበዋል፡፡ በዚህም መልካምስነምግባርን እንዴት ዜጎች መላበስ ይችላሉ ? የሙስናስ ባህሪያት ምንድን ናቸው? ሙስና ከመከሰቱ በፊት ቅድመ መከላከል እንዴት ይደረጋል? የሀይማኖት ተቋማትና ሌሎች የሲቪክ ማህበራትስ ሚና በሚሉትና ተያያዝ ርዕሶች ዙሪያ ኃላፊው በሰነዱ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም ከቤቱ አስተያየትንና ጥያቄ ተነስቶ ምልሽ ተሰጥቶበታል፡፡